Fana: At a Speed of Life!

ነዳጅን ከተቀመጠለት የዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው – አቶ አሕመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ነዳጅን ከተቀመጠለት የዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው አሉ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ።

ሚኒስትሩ የነዳጅ ግብይትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ መንግሥት ለነዳጅ አቅርቦት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ መንግሥት በውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ ድጎማ የሚያደርግበት ነዳጅ ከተቀመጠለት የዋጋ ተመን በላይ በገበያ ላይ እየዋለ መሆኑ በጥናት ተደርሶበታል ነው ያሉት፡፡

ህገ ወጥ ድርጊቱን የፈጸሙ የመንግሥት ተቋማትን ጨምሮ ተባባሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ መጀመሩን አብራርተዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተው ግጭት የነዳጅ አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ የገለጹት ሚኒስትሩ÷ በትናንትናው ዕለት የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያም በዓለም አቀፍ ገበያ ካለው የዋጋ ጭማሪ አንፃር ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የቀውሱ ማብቂያ ያልታወቀ በመሆኑ መንግሥት በቀጣይ በጥናት ላይ የተመሰረተ የቁጠባ ግብይት ስርዓት እንዲተገበር ያደርጋል ብለዋል፡፡

መንግሥት የጀመረው የህግ ማስከበር ስራም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው÷ ዜጎችም ለዚህ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰለሞን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.