መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የመቻልን ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ሽመልስ በቀለ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቅቆ በተጨመረ ደቂቃ እና በ49ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ38 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ አዳማ ከተማ ደግሞ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን ይገጥማል።
እንዲሁም ባሕርዳር ከተማን ከመቐለ 70 እንደርታ የሚያገናኘው ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይደረጋል።