Fana: At a Speed of Life!

የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “ልውቅሽ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩ በሴቶች አትሌት ቤተልሄም አስማረ እንዲሁም በወንዶች ስማቸው ወልዴ አሸንፈዋል።

አትሌት ቤተልሄም አስማረ 1 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቅቃለች።

አትሌት ትነበብ ነጋ እና አትሌት ያተነ ኮረምሼ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ፈጽመዋል።

በወንዶች ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው አትሌት ስማቸው ወልዴ 1 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ7 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ ገብቷል።

አትሌት ጌታቸው ኪዳኔ እና ሱልጣን አብደላ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።

የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ሩጫ በአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም ሃብቶችን ለማስተዋወቅና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.