Fana: At a Speed of Life!

4ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የነበረው 4ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ 1ኛ የወጡ ተወዳዳሪዎች 500 ሺህ ብር፣ 2ኛ ለወጡ 400 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ ለወጡ 300 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የክህሎት ልማት እና የፈጠራ ሥራ የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ብሎም ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማፋጠን ያግዛል፡፡

መንግሥት የፈጠራ ሥራን ለመደገፍ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስታውቀው፤ ለአብነትም የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴርን ከማቋቋም ጀምሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን እያስፋፋ መሆኑን አንስተዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ውድድሮች የክህሎት አስፈላጊነትን በማኅበረሰቡ ዘንድ ለማስረጽ እንደሚረዱም ጠቁመዋል፡፡

የውድድሩ አሸናፊዎች ለሌሎች ወጣቶች አርአያ እንደሚሆኑ ገልጸው፤ የውድድሩ አሸናፊዎች ለሀገራቸው እድገት እና የብልጽግና ጉዞን ለማሳደግ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው፤ 4ኛውዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ካለፉት ዓመታት ከነበሩት ውድድሮች በተሻለ መልኩ የፈጠራ ሥራዎች የታዩበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም ጥራት ያላቸው እና ችግር ፈቺ የሆኑ ምርቶች በስፋት የተወዳደሩበት መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

በቅድስት ብርሃኑ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.