ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሰባት ዓመታት እንደ ሀገር ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት በርካታ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም ላይ ሚኒስትር ዴዔታው እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና ሌሎች ዘርፎች የሪፎርም ሥራ መሠራቱን አንስተዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላት የኢኮኖሚ ግንኙነት መጠናከሩን ገልፀዋል፡፡
መንግሥት ባለፉት ዓመታት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎችን ጨምሮ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑንም አስረድተዋል፡፡
እንደሀገር ማዕድን እና ቱሪዝምን ጨምሮ ባሉን በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ በሚፈለገው ልክ ተግተን ከሠራን የተሻለ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል፡፡
ባለፉት ሰባት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የተመዘገበው ስኬት በዕቅድ እና በቁርጠኝነት በተሠሩ ሥራዎች የተገኘ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ