ምሁራን በሀገራዊ ምክክሩ ሒደት ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል – ም/ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሁራን በሀገራዊ ምክክሩ ሒደት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮምሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት የምሁራን ሚና በሚል መሪ ሃሳብ ከምሁራን ጋር እየተወያየ ነው፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ዋና ኮምሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ÷ በሀገራዊ ምክክሩ ሒደት የምሁራን ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለሀገራዊ ምክክር ሒደት ስኬታማነት ምሁራን የተሳተፉባቸውን የዓለም ሀገራትን የምክክር ሒደት ተሞክሮ መውሰድ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
ስለሆነም ምሁራን በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሒደት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸው ሚና መወጣት እንዳለባቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡
በምክክር ሒደቱ ጠንካራ ሥራዎችን ማበረታታት እና የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማሳየት መፍትሔ መጠቆም እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ