Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በብራዚል-አፍሪካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በ2ኛው የብራዚል-አፍሪካ የምግብ ዋስትና፣ ረሃብን መከላከል እና የገጠር ልማት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚሊያ ዛሬ የተጀመረው ጉባዔው፥ ‎በብራዚልና በአፍሪካ ሀገራት መካከል በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በንግድና በዘላቂ ልማት ዘርፎች ላይ ተጨባጭ እድገት ለማምጣትና ትብብርን ለማጎልበት የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ጉባዔው ‌‎ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ሰፊ ፋይዳ እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡

‎በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ ከጉባዔው ጎን ለጎን ከብራዚል ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኢንዱስትሪና ልማት ሚኒስትር ጀራልድ ሮድርጌዝ አልካሚን ጋር ተወያይቷል።

‎አቶ ተመስገን በዚሁ ወቅት፥ የባለብዙ ወገን ትብብርንና ሌሎች ፈጣን ለውጥ የሚያመጡ አሠራሮችን ለመተግበር በጋራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል።

‎ምክትል ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያን ፈጣን እድገትና በጥሩ መሰረት ላይ የሚገኘውን የሀገር ውስጥ ምርት መነቃቃትን አድንቀዋል፡፡

ሀገራቸው በተለይም ኢትዮጵያ በምትታወቅበት ጠንካራና ዘመናዊ የአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ የመሥራት ፍላጎት እንዳላትም አረጋግጠዋል፡፡

‎በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.