Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ ከተማ ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች አቤል አሰበ በጨዋታ እንዲሁም አስራት ቱንጆ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የባህር ዳር ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ሙጂብ ቃሲም አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ባህርዳር ከተማ በ48 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ድሬዳዋ ከተማ በ36 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ቀን 9 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.