ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ሀድያ ሆሳዕናን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ፀጋዓብ ይግዛው ሲያስቆጥር፤ አቤል ሀብታሙ የኢትዮ ኤሌክትሪክን የአቻነት ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሀድያ ሆሳዕና ተከታታይ ሁለተኛ ጨዋታውን በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቅ፤ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ 5ኛ እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ34 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡