Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኖትረዳም ካቴድራልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራልን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የቅርሱ መጠበቅን ባሕላዊ እና ዓለም አቀፍ ዋጋ ያመላከተ እና ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ትምሕርት የሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

በፈረንጆቹ በ2019 ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ የተደረጉ የጥበቃ ሥራዎች ፈረንሳይ ታሪካዊ ምልክቶቿን ጠብቃ ለመጪ ትውልዶች ለማቆየት ያላትን ፅኑ አቋም የሚያሳዩ ናቸው።

ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጎንደር ፋሲለደስ እስከ አባጅፋር ጅማ ቤተመንግሥት እና በርካታ ቅርሶች ድረስ አቻ የማይገኝለት የታሪክ እና የባሕል ሀብት እንዳላት ሀገር ኢትዮጵያ ሀገራችን የቅርስ ጥበቃ እና እድሳትን ቅድሚያ የምትሰጥበት በርካታ ፀጋ አላት።

ቱሪዝምን ማስፋፋት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቁልፍ የትኩረት መስክ በመሆን በኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ከአምስቱ ምሰሶዎች አንዱ ሆኖ እየተሰራበት እንደሚገኝም የጽ/ቤቱ መረጃ አስታውሷል።

ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተመክሮ በመማር ኢትዮጵያ የባሕል ሀብት ቅርሶቿን የመጠበቅ እና ቀጣይነት ያለው የቱሪዝም ልማት ሥራ ጥረቷን ለማጠናከር ትችላለች ሲልም ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.