ዴቪድ ራያ እና ማትዝ ሰልስ የወርቅ ጓንት አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ እና የኖቲንግሃም ፎረስት ግብ ጠባቂ ማትዝ ሰልስ የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዘመንን የወርቅ ጓንት በጋራ አሸንፈዋል።
ሁለቱ ግብ ጠባቂዎች በውድድር ዓመቱ 13 ጊዜ መረባቸውን ሳያስደፍሩ በመውጣት ነው የወርቅ ጓንቱን ማሸነፍ የቻሉት።
ከብሬንት ፎርድ በውሰት አርሰናልን በተቀላቀለበት የ2023/24 የውድድር ዘመን የወርቅ ጓንቱን ያሸነፈው ዴቪድ ራያ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የወርቅ ጓንቱን ማሸነፍ ችሏል።
እንዲሁም በውድድር ዓመቱ ድንቅ ብቃቱ እያሳየ የሚገኘው የኖቲንግሃም ፎረስት ግብ ጠባቂ ማትዝ ሰልስ የሽልማቱ ተጋሪ ሆኗል።