በዲጂታል የታገዘ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ ሴክተር ልማት ትግበራ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዲጂታል የታገዘ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ ሴክተር ልማት እያከናወነች መሆኗን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ ገለጹ።
51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ተቋም ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።
አቶ ማሞ በዚህ ወቅት፤ እየተከናወነ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የግሉን ዘርፍ በሚያበረታታ እና ኢንቨስትመንትን በሚያረጋግጥ መልኩ በልዩ አመራር እየተተገበረ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በዚህም በፋይናንስ ዘርፉ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን በሚያረጋግጥ መልኩ ሕግ ከማሻሻል ጀምሮ በኢኮኖሚው ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች መሠራታቸውን አንስተዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፋይናንስ ዘርፉ የተሠሩ ሥራዎች የኢንሹራንስ ሴክተሩን ልማት በማገዝ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
ብድር ላይ ያሉ ችግሮች ሲፈቱ ዘርፉን በሚፈለገው ልክ ማሳደግ እንደሚቻልም አስረድተዋል፡፡
በለይኩን አለም