በጋምቤላ ክልል 332 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ስራ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል 2 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 332 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ስራ ጀምረዋል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሎው ኦቦኬ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ500 በላይ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት ባለሀብቶች መካከል 332 ብቻ ስራ መጀመራቸውን ኮሚሽነሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ገልጸዋል፡፡
በተካልኝ ኃይሉ