ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሃዲያ ዞን በገጠር ኮሪደር ሞዴል የመኖሪያ መንደር አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን በገጠር ኮሪደር ሞዴል የመኖሪያ መንደር መርሐ ግብር አስጀምረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፥ በከተማ የተጀመሩ የክረምት በጎ ፍቃድ ልማት ስራዎችን ከገጠሩ ክፍል ጋር የማስተሳሰር አካል በሆነው የገጠር የኮሪደር ልማት ስራ እያስጀመርን ነው ብለዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ዱባንቾ ቀበሌ በገጠር ኮሪደር ሞዴል የአርሶ አደሮች መኖሪያ መንደር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር መካሄዱንም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው፥ እነዚህ ማሳያ መንደሮች መገንባታቸው አርሶ አደሩ የግብርና ስራ እያከናወነ የተሻለ ሕይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።