በናዳ ምክንያት ተዘግቶ የነበረው ከአዲስ ዘመን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድ ተከፍቷል
በናዳው ምክንያት መንገዱ በመዘጋቱ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ የነበረ ሲሆን የሊቦ ከምከም ወረዳ የዞኑ ፀጥታ አካላት የጋራ ትብብር ረፋድ ላይ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ሆኗል።
መንገዱ በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ቋላ ዮሀንስ ከሚባለው ዳገታማ ሥፍራ ላይ ነበር።
በናዳው አንድ ተሽከርካሪ መጠነኛ ጉዳት ሲደርስበት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩን የሊቦ ከምከም ወረዳ የመንገድ ደኅንነት ባለሙያ አሰፋ አስረሳኸኝ ተናግረዋል።
መንገዱ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት ሲሆን ÷ከሱዳን የሚገቡ ተሽከርካሪዎችም በዚሁ መንገድ እንደሚተላለፉም ነው የተነገረው።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።