Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት ተጠናቅቋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ዝግጅት ተጠናቅቋል አለ፡፡

ከፋና ዲጂታል ጋር ቆይታ ያደረጉት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የወረቀት ፈተናዎቹ በየመፈተኛው ማዕከላት ገብተዋል።

በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወሰዱ ተማሪዎች ደግሞ ከሲስተም ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተሰርተው መጠናቀቃቸውን ገልጸው፤ የመብራት እና ኢንተርኔት መቆራረጥ እንዳይከሰት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብበር እየሰራን ነው ብለዋል።

በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች እንዳይቸገሩ ሲስተሙን ለአጠቃቀም ምቹ ከማድረግ ባለፈ በቂ ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

በተጨማሪም የፈተና ማዕከላት የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ጀነሬተር እንዲያዘጋጁ መደረጉን ነው የገለጹት።

ከሰኔ 23 ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የሚያስተባብሩ እና የሚያስፈፅሙ አካላት ወደ ፈተና ማዕከላት መድረሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የፈተና ማዕከላት የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ማዕከላቱ ሲገቡ ከፍተሻ ጀምሮ በጋራ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፈተና ኩረጃ እና ስርቆትን ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው፤ የመፈተኛ ማዕከላት የሆኑ ተቋማትም የፈተና ስርቆት እንዳይኖር አብረውን እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ወደ ፈተና ማዕከላቱ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

 

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.