Fana: At a Speed of Life!

ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 100 ተማሪዎች አስመረቀ።

የዩኒቨርሲቲው 5ኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኢንጅነር አብድልፈታህ አህመድ ራቢ፣ የአካዳሚክና ምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱሰላም አብዱላሂ (ዶ/ር) እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.