Fana: At a Speed of Life!

በ580 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የጅማ ከተማ የተቀናጀ መናኻሪያ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ580 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የጅማ ከተማ የተቀናጀ መናኸሪያ ተመርቋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በዚሁ ወቅት÷ በበጀት ዓመቱ በህዝብ ተሳትፎ እና በመንግስት በጀት በ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ 46 ፕሮጀክቶችን ለመስራት ታቅዶ 43 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል መንገዶች እና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ ኤለን ታምሩ የጅማ ከተማ የተቀናጀ መናኸሪያ ፕሮጀክት ግንባታ በመዘግየቱ ከዚህ ቀደም የነበረውን የኮንስትራክሽን ድርጅት ውል እንዲቋረጥ መደረጉን አስታውሰዋል።

በ2 ነጥብ 17 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የመናኸሪያ ግንባታ በአጠቃላይ 580 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት ገልጸው÷ በአንድ ጊዜ 250 ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተናግረዋል።

በክልሉ ባለፉት 5 ዓመታት በ10 ቢሊየን ብር በጀት የአስፓልት መንገድ ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር ሁሉንም አገልግሎት በአንድነት የያዙ ደረጃቸውን የጠበቁ መናኻሪዎች መገንባታቸውን የብልጽግና ፖርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ ገልጸዋል።

በወርቃፈራው ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.