Fana: At a Speed of Life!

የቤት ልማትና ቱሪዝም ላይ ትኩረት ያደረገ የመንግሥትና የግል አጋርነት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤት ልማትና ቱሪዝም ላይ ትኩረት ያደረገ ሰባት ፕሮጀክቶችን ያቀፈ የመንግሥትና የግል አጋርነት ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ከኦቪድ ግሩፕ፣ ከአይ ሲ ኢ ቤት ልማትና ኮንስትራክሽን፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት፣ ከሰርባ ላንሴት አፍሪካ፣ ከአይሲኤል እና ከፓዮኒር ዲያግኖስቲክ ሴንተር እንዲሁም ከቦስተን ፓርትነር ጋር ተፈራርሟል።

የመንግሥትና የግል አጋርነት ማዕቀፍ የመሰረተ ልማትና የሕዝብ አገልግሎቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መንግሥት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው።

ከፕሮጀክቶቹ መካከል በኦቪድ ግሩፕ፣ በአይሲኢ የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሚከናወኑ ከፊል የጫካ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።

እንዲሁም በቦስተን ፓርትነር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚከናወነው 50 ቅንጡ ማደሪያ ክፍሎችን ያካተተ የአዋሽ ፏፏቴ ሪዞርት፣ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚከናወን የደንቢ ሐይቅ ሎጅ እንዲሁም በሰርባ ላንሴት አፍሪካ፣ ከአይሲኤል እና ከፓዮኒር ዲያግኖስቲክ ሴንተር የሚከወነው የተቀናጀ  የዲያግኖስቲክስ አገልግሎት ማዕከላት ናቸው።

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.