Fana: At a Speed of Life!

ከ600 በላይ ተከሳሾች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ በፌደራል እና በክልሎች ጥፋተኛ የተባሉ 610 ተከሳሾች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡

ብሔራዊ የፍልሰት ዓመታዊ ስብሰባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎች መከላከልና የፍልሰት አስተዳደር ሀገራዊ የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል።

የግንዛቤ እጥረት የክልሎች ቅንጅት ጉድለት፣ በኤጀንሲዎች ላይ የላላ ቁጥጥር መኖር፣ የድንበር አስተዳደር ቅንጅት ጉድለት፣ ተለዋዋጭ የወንጀል አፈጻጸምና ተለዋዋጭ ዓለማቀፍ ሁኔታዎች ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ችግር እንዲስፋፋ ማድረጋቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ከሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ በፌደራል እና በክልሎች ጥፋተኛ የተባሉ 610 ተከሳሾች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት መቀጣታቸውም ተነስቷል፡፡

ከእነዚህ መካከልም በፌደራል ደረጃ 27 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው ከ12 እስከ 25 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

በክልሎች 583 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው ከ10 እስከ 21 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የተፈረደባቸው ሲሆን፥ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

የፖሊሲ የሕግና የትብብር አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ማድረግ የሕጎችን አፈጻጸም መከታተልና ተያያዥ ስራዎችን በመሥራት ለችግሩ የሚመጥን ሥራ መስራት ይጠበቃል።

የፍትህ ሚኒስቴር፣ የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልገሎት እና የስራና ከሕሎት ሚኒስቴር ትብብራቸውን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል በውጭ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ90 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሃገር መመለሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

የውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪትን በተመለከተ 442 ሺህ ዜጎች በሳዑዲ ዓረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች እና ኳታር ለሥራ መሰማራታቸው ተጠቅሷል፡፡

ለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.