Fana: At a Speed of Life!

በጉርሱም ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው ከጉርሱም ወረዳ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በአደጋውም ባጃጁ ውስጥ የነበሩ የ6 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን በወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል መምሪያ ም/ሃላፊ ኢንስፔክተር ቱሪ ድሪባ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

የተከሰተው አደጋ መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በነጌሶ ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.