Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል16 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት 16 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ፡፡

በቢሮው የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደግፌ መለሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ በ2017 በጀት ዓመት 20 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 16 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል፡፡

ገቢው ከመደበኛ ግብር ከፋዮችና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት መሰብሰቡን ጠቁመው÷ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርር የ5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው ብለዋል፡፡

የታክስ አሰባሰብ ሥርዓቱን የማዘመን እና ከቴክኖሎጂ ጋር የማስተሳሰሩ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሃላፊነታቸውን ባልተወጡ 746 ግብር ከፋዮች ላይ በተወሰደ ርምጃ ከ41 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

ያለ ደረሰኝ የሚደረግ የሽያጭ ግብይትን ለመቆጣጠር በተሰሩ ሥራዎች መሻሻሎች ቢኖርም በሚፈለገው ልክ ለውጥ እንዳልመጣ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.