ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በሸካ ዞን የተገነቡ ፕሮጀክቶችን ስራ አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ ሸካ ዞን የተገነቡ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት ስራ አስጀምረዋል፡፡
ወደ ስራ ከገቡ ፕሮጀክቶች መካከል የቴፒ የምርት ጥራት ምርመራና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል አንዱ ሲሆን፥ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በተጨማሪም በዞኑ የኪ ወረዳ የተገነባውን የቡቢ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክትን መርቀው ስራ አስጀመረዋል።
የመስኖ ፕሮጀክቱ ከ37 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ ሲሆን፥ ከ66 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚስችል መሆኑን የክልሉ መስኖ ተቋማት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አሸናፊ ሽብሬ (ኢ/ር) ገልጸዋል።
በህዝብ ተሳትፎና በመንግስት ትብብር ከ12 ሚሊይን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጎጂ ወንዝ ድልድይ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፥ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የቆየውን የህዝብ ችግር እንደሚፈታ ታምኖበታል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንዲሁም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በተስፋዬ ምሬሳ