Fana: At a Speed of Life!

በጉዳያ ቢላ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ ኢፈ ቢያ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው መጠጥ የጫነ ኤፍኤስአር ተሽከርካሪ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ወደ ባኮ ከተማ ሲጓዝ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡

በተፈጠረው አደጋም የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ሃብታሙ አማኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በጉዳያ ቢላ ወረዳ ኢፈ ቢያ ቀበሌ አካባቢ ተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ እንደሚከሰት ጠቁመው÷ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በገላና ተስፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.