በኦሮሚያ ክልል የወባ ስርጭትን ለመግታት በትኩረት እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ የወባ ስርጭትን ለመግታት በትኩረት እየተሰራ ነው አለ፡፡
በቢሮው የበሽታ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ደረጀ አዱኛ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ዞኖችን በመለየት የቅድመ መከላከል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በምዕራብ ወለጋ እና በቄለም ወለጋ ዞኖች በ12 ወረዳዎች የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት እየተከናወነ እንደሆነም ጠቁመዋል።
እየተካሄደ ያለው የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ተጋላጭ ሰዎችን መታደግ እንደሚችል አብራርተዋል፡፡
በጅማ፣ ኢሉ አባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ወለጋ ዞኖች 2 ነጥብ 1 ሚሊየን አጎበር በላይ እየተከፋፈለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለአብነትም በጅማ ዞን የበሽታው ምልክቶች በታዩባቸው ዘጠኝ ወረዳዎች የአጎበር ስርጭት መከናወኑን አንስተዋል።
መድኃኒቶች ለጤና ተቋማት እየቀረቡ መሆኑን ገልፀው፤ ለበሽታው የተጋለጡ ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ መድኃኒት መውሰድ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
በሲፈን መገርሳ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!