Fana: At a Speed of Life!

የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል አሉ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረሀማን።

አፈ ጉባኤዋ ጨፌው የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን እንደሚያደምጥ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ እንደሚወያይ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥራ አፈጻጸም በተለይም ከሥነ ምግባር አንፃር የተሰራውን ሥራ እና በቴክኖሎጂ አስደግፎ ፍትህን ከመስጠት አኳያ የተከናወኑ ተግባራት ይቀርባሉ ነው ያሉት።

ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉ የ2018 ረቂቅ በጀት እና የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

የሰላምና ፀጥታ፣ የልማት ሥራዎች፣ መልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጨፌው በስፋት ከሚወያይባቸው ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረሀማን ገልጸዋል።

በታምራት ደለሊ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.