Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሐዘን መግለጫ መልዕክት ÷ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎቻችን የተሰማኝን ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።

መንግሥት ለተጎጂ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ÷ የጥንቃቄ ተግባራት አስፈላጊ ናቸው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.