Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ታረሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በ2017/18 ምርት ዘመን የመኸር ወቅት 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ታርሷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 187 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዷል።

በዚህም እስካሁን ድረስ በተከናወነው የመኸር ወቅት እርሻ 5 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚሆነውን መሬት እንደታረሰ ጠቅሰው፤ የዕቅዱን 97 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን ከታረሰው ውስጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር የሚሆነው መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈን ተችሏል ብለዋል።

780 ሺህ ሄክታር መሬት በትራክተር እንደታረሰ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማረስ ታቅዷል ነው ያሉት።

በኩታገጠም ለማረስ ከታቀደው ውስጥም ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ቀሪው ማሣ የሰብሎችን የዘር ወቅት በመጠበቅ በዘር እንደሚሸፈን አመልክተዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግ በየደረጃው እስከ ቀበሌ ድረስ በመሄድ ለአርሶ አደሩ ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ አንስተው፤ አርሶ አደሩ እና የግብርና ባለሙያዎች የአረም እና የተባይ ክትትል እና ቁጥጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.