ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
ጨፌው በጉባኤው የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚወያይ ይሆናል።
የተለያዩ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የሰላምና ፀጥታ፣ የልማት ሥራዎች፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳዮች ጨፌው በስፋት የሚወያይባቸው ናቸው።