የኦሮሚያ ክልል የልዩ አዳሪና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የትምህርት ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 3ኛው የኦሮሚያ ክልል የልዩ አዳሪ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፌስቲቫል በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የትምህርት ፌስቲቫሉን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አስጀምረዋል፡፡
“የአእምሮ ችሎታን ከሥራ ጋር ማገናኘት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ፌስቲቫሉ ከሐምሌ 13 እስከ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡
በመርሐ ግብሩ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ዘጠኝ አዳሪ ት/ቤቶች የተወጣጡ ተማሪዎችን ጨምሮ 2 ሺህ ተማሪዎች እና 50 ትምህርት ቤቶች ተሳትፈዋል።
በፌስቲቫሉ የተማሪዎች የፈጠራ አውደ ርዕይ፣ ጥያቄና መልስ እንዲሁም በተማሪዎች የተሰሩ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ለእይታ ይቀርባሉ፡፡
በሲፈን መኮንን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!