Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል – አቶ መሀመድ እድሪስ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል አሉ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ሰላም ሚኒስቴር በጋራ “ሰላምን በማጽናት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የዴሞክራሲ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ መሀመድ እድሪስ በመድረኩ እንዳሉት፥ ከለውጡ ወዲህ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና አዎንታዊ ሰላምን ለማጎልበት ታቅዶ እየተሰራ ነው።

የሰላም ሚኒስቴር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

በተወሰኑ አካባቢዎች ተከስተው የነበሩ ግጭቶችን ለመፍታት ሰላማዊ ውይይትና የህግ ማስከበርን በማከናወን በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ሰላም መስፈኑን መጥቀሳቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎችም ስልጡንና በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን በመፍጠር ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.