የጋራ ምክር ቤቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማዳበር ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማዳበር እየተወጣ ያለውን ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ሰላም ሚኒስቴር በጋራ “ሰላምን በማጽናት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፥ የዳበረ ዴሞክራሲያዊ ባህል በዜጎች ቅቡልነት ላይ የተመሰረተ ሀገረ መንግስት ለመገንባትና ለፖለቲካዊ መረጋጋት ወሳኝ ነው።
ነጻ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት እና ስልጡን የፖለቲካ ምህዳር ለሀገር ልማት ቀጣይነትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሀገሪቱ በሁሉም መስክ ወደ እድገት ጎዳና የምታደርገውን ጉዞ ለማሳካት አስተማማኝ ሰላም በመገንባት ሂደት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ነው ያሉት።
ግጭትን በዘላቂነት ለማስቀረት እና ጠንካራ ዴሞክረሲ ለመገንባት የፖለቲካ ፓርታዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አውስተው፤ የጋራ ምክር ቤቱ የሀገርን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማዳበር እየተወጣ ያለውን የላቀ ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!