Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የሰራችው ስራ የሚደነቅ ነው – አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የሰራችው ስራ የሚደነቅ ነው አሉ።

ዋና ጸሐፊው በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ሰፊ ስራ ሰርታለች።

በተለይም በስንዴ ልማት እና ለአየር ንብረት የማይበገር የግብርና ልማት ላይ ያስመዘገበችው ስኬት የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ለተቀረው ዓለም እንደምሳሌ የሚወሰድ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የምግብ ስርዓትን ሚዛናዊነት ማመጣጠን እንደሚገባ ገልጸው፤ ሁሉም ባለድርሻዎች በትኩረት ሊይዙት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአየር ንብረት ላይ ተገቢውን ስራ መስራትና በዓለም ላይ ሰላምን ማረጋገጥ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤን ለማስተናገድ ላሳየችው ቁርጠኝነትም ምስጋና አቅርበዋል።

በመሳፍንት ብርሌ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.