Fana: At a Speed of Life!

የመደመር አራቱም መጽሐፍት ለነገ መንገድ የሚጠርጉ ናቸው – ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፉት አራቱም የመደመር መጸሐፍት አንዱ አንዱን የሚመራ አሁናዊውን የሚወስን ከትላንቱ የማይጣላ ለነገ መንገድ የሚጠርግ ነው አሉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፡፡

ሚኒስትሯ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት መጸሐፍ ምርቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ሂሳዊ ዳሰሳ አቅርበዋል።

በዳሰሳቸውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፉት መደመር፣ የመደመር መንገድ፣ የመደመር ትውልድ እና የመደመር መንግሥት መጽሐፍት መሰናሰን ላይ ትኩረት አድርገው ፋይዳቸውን አብራርተዋል።

መጽሐፍቱ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን በመለየት የሚጠቁሙ መሆናቸውን ገልጸው፤ ያሳለፍናቸውንና እያሳለፍናቸው ያሉ ችግሮችን ምንጭ ከመደመር ጀምሮ ከነምክንያቱ የሚያስቀምጡ ናቸው ብለዋል።

አብዛኞቹ ችግሮች ከውጪ የተቀዱ የፖለቲካ አስተሳሰቦችን እንደወረደ ለመተግበር ሲሞከር የሚከሰቱ መሆናቸውን በመጽሐፍቱ መመላከታቸውን ተናግረዋል።

ከመደመር መጽሐፍ የጀመረው ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄው አካል የመሆን ጥረት የመጣው ለውጥ ሀገርን የሚለውጥ መሆን እንዳለበት አጽንኦት የሰጠ ነው ብለዋል፡፡

ይህም እስከ መደመር መንግሥት መጽሐፍ ድረስ በነበረው ዘለቄታ መሬት የወረዱ ውጤቶችን አምጥቷል በማለት ገልጸው፤ ውጤቶቹ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚጨበጡ ሆነው መቀመጣቸውን አብራርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.