Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ፍትህ ቢሮ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጥቅም አስከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር ፍትህ ቢሮ የገንዘብ ግምቱ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሆነ የመንግስትና የህዝብ ጥቅም አስከብሯል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ተስፋዬ ደጀኔ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ቢሮው የገንዘብ ግምቱ 5 ቢሊየን 608 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የመንግስት እና የህዝብ ጥቅሞች በፍርድ ቤት እንዲከበር አድርጓል።

እንዲሁም በሌሎች ተከራካሪ አካላት የተያዙ 272 ቤቶች እና 64 ሼዶች ማስመለስ እንዲሁም 260 ነጥብ 32 ሄክታር መሬት በህግ እንዲጠበቁ ተደርጓል ብለዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በፍትሐብሔር ጉዳዮች ከቀረቡ 6 ሺህ 379 መዝገቦች መካከል 3 ሺህ 900 በላይ መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን ነው ኃላፊው ያመለከቱት።

እንዲሁም ሌሎች 25 መዝገቦች በድርድር እልባት እንዲያገኙ እና 2 ሺህ 295 መዝገቦች ደግሞ ወደ 2018 በጀት ዓመት መተላለፋቸውን ጠቁመዋል።

ቢሮው የከተማ አስተዳደሩ ሕጋዊ ወኪል በመሆን በየትኛውም የዳኝነት እርከን በመቅረብ፣ የፍትሐብሔር ክርክር በማድረግ፣ የከተማ ነዋሪውንና የአስተዳደሩን መብትና ጥቅም ማስጠበቁን ተናግረዋል።

የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጡን እንዲሻሻል የራሱን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝም አንስተዋል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.