Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የጅቡቲ ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀና በሁሉም መስክ በምሳሌነት የሚገለጽ ነው-ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 7 ፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ የኢትዮጵያና የጅቡቲ የመንግስት ለመንግስት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀና በሁሉም መስክ በምሳሌነት የሚገለጽ መሆኑን ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ኦማር ጌሌ ይህንን የገለጹትበጅቡቲ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን በቅርቡ የተሾሙት አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ለፕሬዚዳንቱ በትናንትናው እለት የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።

አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በቆይታቸው የሁለቱን አገራት ህዝቦች የቆየ ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ተናገረዋል።

አያይዘውም ከጅቡቲ መንግስትና ህዝብ ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛና ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጅቡቲውፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በበኩላቸው÷ የጅቡቲ መንግስት የሁሉቱን አገራት ሁሉን አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያና የጅቡቲ የመንግስት ለመንግስት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀና በሁሉም መስክ በምሳሌነት የሚገለጽ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ለአምባሳደሩ ለስራቸው መሳካት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም በዚህ ወቅት አረጋግጠዋል።

አምባሳደሩ በቆይታቸው የሁሉቱን አገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ እምነታቸው መሆኑንም ፕሬዚዳንት ጌሌ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.