Fana: At a Speed of Life!

መዲናዋ በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ዕቅድ ለመሳተፍ ተዘጋጅታለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት በሚካሄደው በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ ዕቅድ ለመሳተፍ ዝግጁ ሆኗል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

በዕለቱ ችግኞችን በመትከል አንድነታችንን፣ ቁርጠኝነታችንን እና ፅናታችንን እናሳያለን ብለዋል።

የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ ዕድሜ ፣ ብሔር፣ ኃይማኖት፣ የኑሮ ደረጃ ሳይለያቸው ነገ ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የያዘችዉን እቅድ ለማሳካት፣ በአራቱም አቅጣጫ ድርሻችን በነቂስ እንነሳለን ነው ያሉት።

ያለፉት 6 አመታት ገድል በነገዉ ዕለትም ይደገማል ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ አዲስ አበባ በዕለቱ ዳግም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል አንድነታችንን፣ ቁርጠኝነታችንን እና ፅናታችንን የምናሳይበት ዕለት ይሆናል ማለታቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.