Fana: At a Speed of Life!

225 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 225 ሺህ የቀረሶ ዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ ተጨምረዋል አለ የባሕር ዳር ዓሳና ሌሎች የውሃ ውስጥ ሕይወት ምርምር ማዕከል፡፡

የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ እርቅይሁን አስማር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷በጣና ሐይቅ ያለውን የዓሳ ሃብት ይበልጥ ለማሳደግ የተሻሻሉ የዓሳ ዝርያዎችን ወደ ሐይቁ የመጨመር ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

አሁን ላይ እየቀነሰ የመጣውን የዓሳ ሃብት ለማጠናከርና የሕብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በምርምር የተሻሻሉ የዓሳ ዝርያዎችን በማባዛት የዓሳ ጫጩቶችን ወደ ጣና እና ሌሎች ውሃማ አካላት የመጨመሩ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የዓሳ ጫጩቶች መባዛታቸው ጠቅሰው÷ ከዚህ ውስጥም የዛሬውን ጨምሮ 312 ሺህ በላይ የቀረሶ ዓሳ ጫጩቶች ወደ ጣና ሐይቅ ተጨምረዋል ነው ያሉት፡፡

ቀሪው የዓሳ ጫጩትም ወደ አርሶ አደሩ ኩሬና ልዩ ልዩ የውሃማ አካላት ከመሰራጨቱ ባለፈ ለምርምር አገልግሎት መዋሉን አስገንዝበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.