Fana: At a Speed of Life!

አቶ አህመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ማምታ ሙርቲ ጋር በሰው ሀብት ልማት ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት፣ ለጤና ጥበቃ፣ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስና የሴፍቲኔት ተደራሽነትን ለማስፋት እያደረገች ያለውን ጥረት በተመለከተ ለምክትል ፕሬዚዳንቷ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በትምህርት፣ በክህሎት ልማት፣ በጤናና የሰው ሀብት ልማት እንዲሁም የሴፍቲኔት መርሐ ግብርን ለማሻሻል ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ በበኩላቸው ባንኩ የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር እንዲሁም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.