Fana: At a Speed of Life!

በተኪ ምርቶች ላይ በተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት በተኪ ምርቶች ላይ በተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ማዳን ተችሏል አለ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፡፡

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮቤል አሕመድ እንዳሉት ÷ የኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ይበልጥ ለማጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡

በተለይም አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በተኪ ምርች ላይ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የአምራች ዘርፉን የአሰራር ሥርዓት ለማሻሻል በትብብር መሰራቱን ጠቁመው ÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች 59 ነጥብ 89 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረትና ለገበያ በማቅረብም ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን አቶ ሮቤል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለ2 ሺህ 231 አምራች ኢንተርፕራይዞች ጠንካራ የገበያ ትስስር በመፍጠር ገቢ ምርቶችን እንዲተኩ በትኩረት መሰራቱን አመልክተዋል፡፡

357 አምራች ኢንተርፕራይዞች 38 ሺህ 317 ቶን ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን ወደ ውጭ በመላክ 59 ነጥብ 89 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም ጠቁመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.