ዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ሥነ ምሕዳርን መጠበቅ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 28፣ (ኤፍ ኤም ሲ) አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እፅዋትን በመጠበቅ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እየሰራሁ ነው አለ፡፡
በዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ዳይሬክተር ሽቴ ጋተው (ዶ/ር) ÷ በመጥፋት ላይ ያሉ የእፅዋት ዝርያዎችን ከተለያዩ አካባቢዎች በማምጣት ጥበቃና የልማት ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ከመድሃኒትነት ጀምሮ ለምግብነት የሚያገለግሉ እና ለአካባቢ ሥነ ምሕዳር ወሳኝ የሆኑ እፅዋትን በመጠበቅ ረገድ ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡
ዩኒቨርሲቲው የምርምር ሥራዎችን ከማከናወን ባለፈ በተለያዩ ዘርፎች ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ነው ያብራሩት፡፡
ለሥራው ውጤታማነትም የኢትዮጰያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመልክተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቱው መሰል ሥራዎችን በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች እየከወነ እንደሚገኝ ጠቁመው÷ በቀጣይ ሥራውን በዩኒቨርሲቲውና ተባባሪ አካላት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!