Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት በዲዛይኑ ባካተታቸው ይዘቶች ለዓለምአቀፍ እውቅና ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በቅርቡ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት በዲዛይኑ ውስጥ ባካተታቸው ይዘቶች ለዓለምአቀፍ እውቅና ተመርጧል፡፡

የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት ጥብቅ የደህንነት ባህርያትንና ምስጢራዊነትን በመያዝ፣ የላቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀምና የተጠቃሚውን ማንነት የሚለዩ ሁለንተናዊ ወሳኝ መረጃዎችን ሰንዶ በማካተቱ ነው ለሽልማት የተመረጠው፡፡

የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት ለሽልማት የተመረጠው በንድፍና ፈጠራ ልዩ ሽልማትና እውቅና በመስጠት በሚታወቀው ሬድ ዶት ብራንድስ እና ኮሙኒኬሽን መሆኑ ታውቋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ድንቅ መለያ የሆኑ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን በውስጡ ያካተተ መሆኑ ለዚህ እውቅና እንዳበቃው አገልግሎቱ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.