Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በወረዳው መስቀል በር ቀበሌ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት ከሟቾች በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው ትናንት ነሐሴ 2/2017ዓ.ም ሌሊት የደረሰ ሲሆን፥ በንብረትና በተዘሩ ሰብሎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው የሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ታለፈ ተናግረዋል፡፡

የክረምት ወቅት እንደመሆኑ ማህበረሰቡ የጎርፍ መፋሰሻ የሆኑ መሬቶችን በማፅዳትና ከጎርፍ ማፋሰሻ ቦታዎች በመራቅ ራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአበበ የሸዋ ልዑል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.