የጤና ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማዘመን እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማዘመን እየተሰራ ነው አለ የጤና ሚኒስቴር፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሐረሪ ክልል የተለያዩ የጤና ተቋማትን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በክልሉ በጤናው ዘርፍ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመታገዝ እየተሰሩ የሚገኙ አበረታች ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በተለይም በጁገል ሆስፒታል በዲጂታል ኤክስሬይና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመታገዝ የሚሰጠው አገልግሎት ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የጤና ዘርፉን ሁለንተናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡
በተስፋዬ ሃይሉ