Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ወደ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ሊገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ሊገቡ ነው።
በቢሮው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ዳኛቸው ሽፈራው አዲስ አበባ ከወረቀት የተላቀቀ አገልግሎትን ለመገንባት የስማርት ሲቲ ጉዞ ላይ እንደመሆኗ ተቋሙ ዘርፉን ለማዘመን የሚያስችሉ የተለያዩ ዲጂታል አሰራሮችን ጀምሯል ነው ያሉት።
ቢሮው የትራንስፖርት ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ በቬሎሲቲና በከተማ አውቶብሶች መጀመሩን ጠቅሰው፤ ተቋማቱ በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የብዙኃን ትራንስፖርት የሚሰጡ የከተማ አውቶብሶችን ጨምሮ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች ወደ ዲጂታል ክፍያ እንደሚገቡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.