Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአርቲስት ደበበ እሸቱ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርቲስት ደበበ እሸቱ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ ÷በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያሳረፈው አርቲስት ደበበ እሸቱ በማረፉ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።

ደበበ እሸቱ ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ቴአትርና ፊልም ዕድገት ፋና ወጊ ከሆኑት ልሂቃን አንዱ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ በጽናት እንድታሳካ በኪነ ጥበብ ተሰጥዖው ያበረከተውን ሚና ዘወትር ስናስታውሰው እንኖራለን ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.