Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት መህሪባን አሊዬቫ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት መህሪባን አሊዬቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር) ጋር በአዘርባጃን በካሄድነው ጉብኝት ወቅት ከአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት መህሪባን አሊዬቫ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርጌያለሁ ብለዋል።

በውይይቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በሚሰሩ ተጋላጭ ማህበረሰቦች በተለይም ሴቶች፣ ሕፃናት እና የአካል ጉዳተኞች ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

በማህበራዊ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተናል ያሉት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው÷ የአዘርባጃን ቀዳማዊት እመቤት ተዛማጅ ማዕከላትን በመገንባትና የክህሎት ስልጠና በማመቻቸት ረገድ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በአዘርባጃን መዲና ባኩ አቅራቢያ ያለውን የአርኪኦሎጂና የባህል ሙዚየም እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች የእደ ጥበብ ማምረቻ ማዕከልን መጎብኘታቸውን ጠቅሰዋል።

በጉብኝቱ በቢሮአችን በተጋላጭ ዜጎች ላይ የምንሰራውን ሥራ ለማጠናከር ጠቃሚ ልምድ አግኝቸበታለሁ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.