Fana: At a Speed of Life!

በለንደን ደርቢ ቼልሲና ክሪስታል ፓላስ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንደኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሁለቱ የለንደን ክለቦች ቼልሲ እና ክሪስታል ፓላስ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ የኖቲንግሃም ፎረስትና ብሬንትፎርድ ጨዋታ ባለሜዳው ፎረስት ብሬንትፎርድን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡

የኖቲንግሃም ፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች ክሪስውድና ንዶዬ ሲያስቆጥሩ÷ የብሬንትፎርድን ብቸኛ ግብ ኢጎር ቲያጎ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

ከደቂቃዎች በኋላ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.