የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህድስና እና ሒሳብ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 28 የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ተማሪዎቹ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ናቸው።
ስልጠናው ተማሪዎቹን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ ትምህርት መስኮች ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ያለመ ነው።
ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ ሲሰጥ በቆየው ስልጠና የተማሪዎቹን የላቀ ውጤት የማምጣት ዕድል እና የከፍተኛ ትምህርት ፍላጎትን ማሳደጉ ተነግሯል።
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ከ50 በላይ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁ ይታወሳል።
በመራኦል ከድር