Fana: At a Speed of Life!

ከተረጂነት ለመላቀቅ በግብርና ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው – አቶ አዲሱ አረጋ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና አሰራርና የአስተራረስ ዘይቤን በማዘመን ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ተግባራት በግብርና ዘርፍ ኢንሼቲቮች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው አሉ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ።
የግብርና ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ውይይት በአዳማ እየተካሄደ ነው።
አቶ አዲሱ አረጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ተግባራት በግብርና ዘርፍ ኢንሼቲቮች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው።
በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመኸርና በበልግ ሰብል ልማት፣ በቡና፣ በወተት ላሞችና በዓሣ ሃብት ልማት ከተገመተው በላይ ስኬት መመዝገቡን ጠቅሰዋል።
በመኸርና በበጋ መስኖ ስንዴ ላይ በተሰራው ስራ በየዓመቱ ከውጭ ይገባ የነበረን ከ17 ሚሊየን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ማስቀረት መቻሉን ተናግረዋል።
በቢራ ገብስ ላይ በተከናወነ ሥራ ከውጭ ይገባ የነበረን ምርት በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ጠቁመው÷ ሥራው ትልቅ ውጤት የተገኘበትና ዓለም አቀፍ ልምድ የተቀሰመበት መሆኑን አብራርተዋል።
በተመሳሳይ ከውጭ የሚገባውን የሩዝ ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት የተጀመረው ርብርብ ይጠናከራል ነው ያሉት፡፡
ግብርናን በማዘመን ረገድ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት ሚኒስትሩ ÷ ለዚህም የሜካናይዜሽን እርሻን ማስፋፋትና የኩታ ገጠም አስተራረስ ሥነ ዘዴን መጠቀም ላይ ትኩረት እንደሚደረግ መናገራቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.